Thank you for your participation in our kickoff event on April 9, 2022!
ለተሳትፎዎ ከልብ እናመሰናለን!
መድኅን ለወገን የምስጋናና የትውውቅ መርሃግብር ላይ የተሰጠ
ጋዜጣዊ መግለጫ
መድኅን ለወገን በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዎ በምንኖር ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጥቅምት 2013 ዓ.ም. የተመሰረተ የበጎ አድርራጎት ድርጅት ነው። ይህንንም ተግባሪዊ ለማድረግ በሜሪላድ ግዛት የ501C እውቅና በማግኘት ተመዝገበን በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን።
የመድኅን ለወገን ዋና ዓላማ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን በችግራቸው ጊዜ በመገኘት መታደግ ሲሆን ከማንኛውም የሃይማኖት፣ የዘርና የፖለቲካ ተጽዕኖ ነጻ የሆነ ሰብአዊ ድርጅት ነው።
መድኅን ለወገን አመሰራረቱም ከላይ የተጠቀሰውን ዓላማ በማንገብ የኮቪድ 19ን ወረርሽኝና የኢኮኖሚ ቀውስን ተከትሎ ቤሩት ሊባኖስ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የተከሰተው እንግልት ለመታደግ ነበር። በአሜሪካና በተለያዩ የውጪ ሀገራች ሚገኙትን ወገኖቻችንን በማስተባበር 105 እህቶቻችንን ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ሙሉ የመሳፈሪያ ወጪያቸውን በመሸፈን ነው። በመሆኑም ይህን ተሞክሮአችንን በመገንዘብ ሰባት ግለሰቦችና የገንዘብና የሃሳብ ድጋፍ ያደረጉ ወገኖች አነስሽነት ተቋቋመ።
በመቀጠልም በአሁኑም ወቅት በሃገራችን በደረሰው ሰብአዊ ቀውስ ለወገኖቻችን ለመድረስ በተከታታይ በኖቬምበር እና ዲሴምበር 2021 በደብረብሃን ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖቻችን ከተለያዮ የአለም ክፍሎች የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በማስተባበር ከ1 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ በማሰባሰብ ዱቄትና አልሚ ምግብ አቅርበናል። የእነዚህ ምርቶች ግዢ ከሃገር ውስጥ ድርጅቶች በመፈጸሙ ግብይቱ በቀጥታ ወደ ባንክ በማስተላለፍ የውጭ ምንዛሪን ለሃገራችን ከማስገኘቱም ባሻገር የሃገር ውስጥ ገበያና ምርትን ያበረታታል።
በቀጣይነትም በጦርነቱ የወደሙ የትምህርት ተቋሞች ላይ በማተኮር በተለይም የወደፊቷን ኢትዮጵያ ተረካቢዎችን ለመቅረጽ በትምህርት ዘርፍ ላይ ለመስራት እቅድ ይዘን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ውይይት ጀምረናል።
ወደፊትም በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በመክፈት ሃገራችንና ወገኖቻችንን በቅርበት የመደገፍ እቅድ ይዘናል።
ዋሽንግተን ዲሲ - ሚያዝያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም./April 9, 2022